37

807

Musica creata da Getu Shanko con Suno AI

37
v4

@Getu Shanko

37
v4

@Getu Shanko

Testi
አንበሳ መርጦ እንጂ
ያየውን በሙሉ አይመለከትም፣
ሁለት ጥንቸል አዳኝ አንዷንም አይዝም
ሁለት ጥንቸል አዳኝ አንዷንም አይዝም።

በብልሆች አገር ሞኛሞኝ ገበሬ
ጠምደህ ልረስ አትበል በሬና ጉማሬ።

ሁለት እግር አለኝ ሁለት ዛፍ ወጣለሁ
ብሎ ከሚናገር
ፈጣሪ አታውለኝ አጉል ከሆነ ሰው።

ባዋሉህ ቦታ ዋል ባስቀመጡት ስፍራ
ሲያከብዱህ አትቅለል አትሁን ገለባ።

ሀሉ አማረችኝ ሰው ዓላማ የሌለው
ሲመኝ እየኖረ ሲመኝ ነው 'ሚሞተው።

ያላየው የታየው
በዚህ አለፈች ብሎ መንገድ ስላሳተው
ጊደር ለጠፋበት ጊደሩን ከፈለው።

በዕድሜው ልክ የማይኖር አንዳንድ ሰው አለ
በጥሬው የሚገኝ ሲሉት ሸመገለ።

አንበሳ መርጦ እንጂ
ያየውን በሙሉ አይመለከትም
ሁለት ጥንቸል አዳኝ አንዷንም አይዝም
ሁለት ጥንቸል አዳኝ አንዷንም አይዝም።

አንዳንድ ሰው አለ የሌለው ቁም ነገር
በሠውነት ሚዛን መለኪያ ሲሰፈር።

አንዳንድ ሰው አለ ላምላኩ ያስቸገረ
ግራ የሚያጋባ-
ማታ የጠየቀውን ሲነጋ እየረሳ።

አንዳንድ ሰው አለ ለቃሉ ያልታመነ
ባለው የማይገኝ-
መልኩና ምግባሩ ያልተገጣጠመ።

አንዳንድ ሠው አለ የሠው አልባሌ
በማር ሲመስሉት ሲቀመስ ኮምጣጤ።
Stile di musica
Ethio jaxx,male,slow,piano and saxphone touch

Potrebbe piacerti

Copertina della canzone Kincses Tábor
v4

Creato da Vira Réka Nickel con Suno AI

Copertina della canzone اريد
v4

Creato da مراد الكربي con Suno AI

Copertina della canzone 여야서회
v4

Creato da HeeJoong Park (VISC) con Suno AI

Playlist correlata

Copertina della canzone Непререкаем Суверен
v4

Creato da Анатолий Волков con Suno AI

Copertina della canzone Ostatni kurs
v5

Creato da Jerzyna K con Suno AI

Copertina della canzone Zente
v4

Creato da Zoltán Tóth con Suno AI